Maryland Issues COVID-19 Fact Sheet in Amharic for Ethiopian Community

The Maryland Department of Health has published coronavirus directive in Amharic for its Ethiopian residents. (Photo: WMDT)

Tadias Magazine

By Tadias Staff

Published: March 27th, 2020

New York (TADIAS) — The state of Maryland Department of Health has issued a COVID-19 Fact Sheet in Amharic for its large Ethiopian community.

You can read the directive below or view the PDF here.

Maryland Department of Health:

ኮሮና ቫይረስ በሽታ 2019 (COVID-19)
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
መጨረሻ አርትኦት የተደረገው ማርች 6 2020

ሀገረ ገዢው ላሪ ሆጋን በሰጡት በመመሪያ መሰረት ወኪሎች ሁሉን አቀፍ እና የተቀናጀ የመከላከል እና ምላሽ የመስጠት እቅዳቸውን ለ ኮሮና ቫየረስ 2019 (COVID-19) መስጠታቸውን ቀጥለዋል።

የሜሪላንድ ጤና ዲፓርትመንት (MDH) ከህዝቡ ጋር ግንኙነት ማድረግ የሚቀጥል ሲሆን ይህ ሁኔታ ያለበት ደረጃ በማሳወቅ እና ትክክለኛ የሆኑ መረጃዎችን በመስጠት ሲሆን ይህም ራስዎን እና ቤተሰብዎን እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ እንዲያውቁ የሚያደርገ ነው።

COVID-19 ምንድን ነው?

COVID-19 የመተንፈሻ አካላትን በሚያጠቃ ቫይረስ የሚከሰት ሲሆን መጀመሪያ ላይ የተከሰተው ዉሀን፣ ሁቤ ወረዳ ቻይና ውስጥ በዲሴምበር 2019 ነው። COVID-19 አዲስ እና በሰዎች ላይ ህመም ፈጥሮ የማያውቅ በሽታ ነው። በመላው አለም COVID-19 በሺዎች የሚቆጠር በሰዎች ላይ ኢንፌክሽን እና ህመም እንዲፈጠር እና በአንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ ሞት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል። በሽታው በመላው አለም የተዛመተ ሲሆን በየቀኑ አዳዲስ የመበከል ሪፖርቶች ይወጣሉ።

COVID-19 አሜርካ ውስጥ ተፈጥሯል?

COVID-19 አሜርካ ውስጥ የተሰራጨ ሲሆን አንዳንድ ሰዎች እንዲታመሙ አድርጓል፣ በአንዳንድ ከባድ ሁኔታዎች ውስጥ ደግሞ ሞት እንዲፈጠር አድርጓል።

አብዛኛዎቹ የተረጋገጡ ህመሞች ብዙ የ COVID-19 ታማሚዎች ወዳሉበት ሀገር በአለም አቀፍ ደረጃ ጉዞ ካደረጉ ሰዎች ሲሆን፣ አሜርካ ውስጥ አንዳንድ የስርጭት ሪፖርቶች ተደርገዋል። “የማህበረሰብ ስርጭት” ማለት በአንድ አካባቢ ላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ማለት ሲሆን፣ ይህም እንዴት ወይም ከየት እንደተያዙ የማያውቁ ሰዎችንም የሚያካትት ነው።

በህዝቡ ላይ ያለው ስጋት ምንድን ነው?

በአንድ ነጥብ ላይ COVID-19 በከባድ ሁኔታ አሜርካ ውስጥ ሊሰራጭ የሚችልበት እድል አለ። ባለሞያዎች በሚመጡት ሳምንታት እና ወራት ውስጥ አሜርካ ውስጥ እና በመላው አለም ተጨማሪ የኮሮኖ ቫይረስ ክስተቶችን መጠበቅ እንዳለብን አሳውቀዋል።

ጉንፋን እን ኢንፍሉዌንዛ የሚተላለፉት በማህበረሰብ ስርጭት ሲሆን – ይህም ማለት ሰዎች እለታዊ ሕይወታቸውን በሚመሩበት ወቅት ከአንድ ሰው ወደሌላው ይተላለፋል ማለት ነው ሪፖርት የተደረገ የ COVID19 ማህበረሰባዊ ስርጭት ተጽኖ ስር ያሉ ማህበረሰቦችን ወዲያው ሊደርስባቸው የሚችለውን ስጋት ከፍ ያደርገዋል።

አሁን ሜሪላንድ ውስጥ በዚህ አዲስ ቫይረስ የተያዘ ሰው አለ?

በማርች 5 2020 ላይ ሜሪላንድ ወስጥ ሶሰት የተረጋገጡ የ COVID-19 ክስተቶች እንደነበሩ ሪፖርት ተደርጓል። ታካሚዎቹ በቫይረሱ የተጠቁት ከሀገር ውጨ ባደረጉት ጉዞ ወቅት ሲሆን፣ አሁን በመልካም ሁኔታ ላይ እና አሁን ለይቶ በማያቆያ ውስጥ በየቤቶቻቸው ይገኛሉ።

ማርች 5 ላይ ሀገረ ገዢው ሆጋን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተጨማሪ በክልሉ ውስጥ ያሉ ግብአቶችን ለመሰባሰብ አውጀዋል። The declaration officially authorized and directed the አዋጁ ለ MDH እና ለሜሪላንድ ድንገተኛ ጊዜ አስተዳደር ወኪል (MEMA) በሁሉም የክልል እና አካባቢ ወኪሎች መካከል ያለውን ትብብር እንዲያሳልጥ ስልጣን እና ትዛዝ የሰጠ ነው። በተጨማሪም አዋጁ MDH እና MEMA በክልላችን እና በአካባቢያዊ ጤና ክፍሎች እንዲሁም ድንገተኛ አስተዳደር ክፍሎች ውስጥ ያለውን ትብብር ያሳልጥ ዘንድ ያስችለዋል።

ትክክለኛ መረጃዎች ስለ ምርመራ እና የክስተት ቁጥሮች በ health.maryland.gov/coronavirus ላይ ይገኛል። ገጹ በየቀኑ አዳዲስ መረጃዎችን ያወጣል።

በዚህ ሰአት ስጋት ላይ ያለው ማን ነው?

በአሁን ሰአት የሚከተሉት ሰዎች ስጋት ውስጥ ናቸው፡
• ስጋት ወዳለባቸው ቦታዎች ጉዞ ያደረጉ
• COVID-19 ካለበት ሰው ጋር የቅርብ የሆነ የግል ግንኙነት ያላቸው
• COVID-19 ያለባቸውን ሰዎች የሚንከባከቡ

COVID-19 የሚሰራጨው እንዴት ነው?

COVID-19 ልክ እንደጉንፋን ወይም ኢንፍሉዌንዛ በሚከተሉት መንገዶች ሊሰራጭ እንደሚችል ይታሰባል፡

• ማሳል እና ማስነጠስ፣ ይህም የትንፋሽ ጥቃቅን ነጠብጣቦችን ይፈጥራል
• የቅርብ የሆነ አካላዊ ግንኙነት ይህም እንደመንካት እና እጅ መጨባበጥ
• ቫይረሱ ያለበትን ቁስ ወይም እቃ መንካት

የ COVID-19 ምልክቶች ምንድን ናቸው?

• ትኩሳት
• ማሳል
• የትንፋሽ ማጠር
• በጣም ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ፣ ኒውሞኒያ (የሳምባ ምች)

COVID-19 አለብኝ ብዬ የማስብ እንደሆነ ምን ማድረግ አለብኝ?

የ COVID-19 ሰጋት ወዳለበት ማንኛውም አካባቢ ጉዞ አድርገው የሆነ እንደሆነ ወይም COVID-19 ካለበት ሰው ጋር ግንኙነት አድርገው የነበር እንደሆነ በተጨማሪም ትኩሳት ሳል ወይም የመተንፈስ ሁኔታ አዳጋች ከሆነብዎ፣ ወዲያውኑ የጤና ምርመራ ያድርጉ። የሚከተሉትን እርምጃዎች ይውሰዱ፡

• ከመሄድዎ በፊት ለሀኪምዎ ወይም የድንገተኛ አገልግሎት ሰጪዎ ይደውሉ
• በቅርብ ስላደረጉት ጉዞ እና የቅርብ ንክኪዎትን (ይህም ቤት ውስጥ ያሉትን ሰዎች ጨምሮ ማለት ነው) ምን እንደነበሩ ያሳውቁ
• ማግኘት የሚችሉ እንደሆነ ጭምብል ያድርጉ

አንድ ሰው COVID-19 ከያዘው ምን ይፈጠራል?

አብዛኛዎቹ ሰዎች ከዚህ ኢንፌክሽን ይፈወሳሉ። አብዛኛዎቹ ሰዎች ዝቅተኛ ወይም ከበድ ያለ ምልክት ያሳያሉ። አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን ቤት ውስጥ ለይተው እንዲያገግሙ ሊመከሩ ይችላሉ። እነዚህ ሰዎች ምልክቶቻቸው እየተባባሱ ከመጡ ለሀኪሞቻቸው ወይም የጤና አገልግሎት ሰጪዎቻቸው መደወል አለባቸው።

አንዳንድ የ COVID-19 ኢንፌክሽኖች ከባድ ህመም ወይም በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ ደግሞ ሞትን ያስክትላሉ። አንድ ሰው ከባድ የሆነ ህመም በ COVID-19 ምክንያት ካጋጠመው ሆስፒታል ውስጥ እንዲተኛ ይደረጋል። አረጋውያንን እና ቀድሞ ሌላ የጤና ችግር የነበረባቸው ሰዎች ከባድ ህመም ለመታመም ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው። ቀድመው የነበሩ የጤና ስጋት ምሳሌዎች የሚከተሉት ናቸው፡ ካንሰር፣ ስኳር፣ የልብ በሽታ ወይም ሌሎች በሽታ የመከላከል እና ጀርሞችን የመዋጋት አቅምን የሚጎዱ በሽታዎች።

ወደ ውጨ ሀገር የመሄድ እቅዴን ማቆም አለብኝ?

የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማእከል (CDC) የጉዞ አማካሪዎችን ማስጠንቀቂያዎች እያደሰ ነው። CDC የግድ አስፈላጊ ያልሆኑ ጉዞዎችን ወደ አንዳንድ ቦታዎች ከማድግ እንዲቆጡ ይመክራል። የጤና ሁኔታዎች አስተማማኝ ያልሆነ ሰዎች የግዴታ ያልሆኑ ጉዞዎችን ወደ አንዳንድ ቦታዎች ከማድረግ እንዲቆጠቡ ይመከራል።

የ CDC ን የጉዞ ማማከር ድረገጽ በመጎብኘት ወደውጪ ሀገር የጉዞ እቅድ እያደረጉ ከሆነ ማስጠንቀቂያዎችን ማየት ይችላሉ፡ https://www.cdc.gov/coronavirus/2019-ncov/travelers/index.html.

ከቤት ወጥቼ ማህበረሰቡን የምቀላቀል ከሆነ ከሆነ የፊት ጭምብል ማድረግ አለብኝ?

የለብዎትም። ከቤት የሚወጡ ከሆነ የፊት ጭምብሎች አይመከሩም ነገር ግን በአንዳንደ መቼቶች ውስጥ የፊት ጭምብሎች ይጠቅማሉ – ይህም እንደ ሆስፒታል ወይም የክሊኒክ መቆያ ክፍል – ሲሆን የመተንፈሻ አካላት በሽታ ከአንድ ሰው ወደሌላኛው አንዳይተላለፍ ማለት ነው።

COVID-19ን ጨምሮ ከመተንፈሻ አካላት በሽታ ሰዎች ራሳቸውን መከላከል ይችሉ ዘንድ የፊት ጭምብል እንዲያደርጉ CDC አይመክርም። የፊት ጭምብል ማድረግ ያለብዎ የጤና ባለሞያ የሚመክርዎ ከሆነ ብቻ ነው። COVID-19 ያለባቸው እና ምልክቱ ያለባቸው ሰዎች የፊት ጭምብል መጠቀም አለባቸው። ይህም ሌሎች ሰዎች አንዲያዙ የሚያደርጋቸውን እድል ለመቀነስ ነው። COVID-19 ያለበትን ሰው በቅርብ ሆነው የሚንከባከቡ ሰዎችም የፊት ጭምብል በቅርብ ርቅት ውስጥ ከሆኑ ማድረግ አለባቸው (ይህም በቤት ወይም በጤና እንክብካቤ ማእከል ወስጥ ሊሆን ይችላል)።

ራሴን እና ሌሎችን ለመጠበቅ ምን ማድረግ እችላለሁ?

እንደ ኢንፍሉዌንዛ እና ጉንፋን አይነት በሽታዎችን ስርጭት ለመከላከል ያስችል ዘንድ በየእለቱ መደረግ ያለባቸውን የመከላከል እርምጃዎችን ይውሰዱ፡

• በሳሙና እና ትኩስ ውሀ ቢያንስ ለ 2 ሰከንዶች እጅዎትን ይታጠቡ
• ቢያንስ 60 በመቶ አልኮል ያለባቸውን የእጅ ጽዳት ምርቶች ሳሙና እና ውሀ የሌለ ከሆነ ይጠቀሙ
• ሳል እና ማስነጠስዎን በእጅዎ በሶፍት ወረቀት ወይም በእጅዎ ክርን ይከልሉ
• አይንዎን አፍንጫዎን እና አፍዎን አይንኩ
• ብዙ ጊዜ በእጅ የሚነኩ እቃዎችን ያጽዱ ወይም መስፈርት የሆኑ የጽዳት ደረጃዎችን በመጠቀም ኢንፌክሽን ያስወግዱ
• ከታመሙ ሰዎች ጋር የቅርብ የሆነን ግንኙነት ያስወግዱ
• ከታመሙ እቤት ይቆዩ፣ ይህም የጤና አገልግሎት ለመፈለግ ከመውጣት ውጪ ማለት ነው

ለ COVID-19 ማግኘት የምችለው ክትባት ወይም መድሀኒት አለ?

የለም ምክንያቱም COVID-19 አዲስ በሽታ ስለሆነ ነው። ነገር ግን፣ ብዙ ባለሞያዎች ለመፈብረክ እየሰሩ ነው። እንደማንኛውም ክትባት ደህንነቱ አስተማማኝ እና ውጤታማ መሆኑን ለመፈተሽ መሞከር አለበት። የ COVID19 ክትባት ዝግጁ እስከሚሆን ድረስ ከአንድ አመት በላይ ሊፈጅ ይችላል።

COVID-19ን የሚፈውስ ምንም አይነት መድሀኒት በዚህ ሰአት የለም። ነገር ግን COVID-19 ያለባቸው ሰዎች የምልክታቸውን ከባድነት ለማስቀነስ የጤና እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል።

ለ COVID-19 እንዴት ዝግጁ ልሆን እችላለሁ?

• በቂ የሆኑ በትዛዝ የማይገዙ መድኒቶችን እና ሌሎች የጤና ግብአቶችን ይህም እንደ ህመም ማስወገጃ፣ የሆድ፣ ሳል እና ጉንፋን መድሀኒቶችን በበቂ መጠን በእጅዎ ላይ አድርገው ያቆዩ
• የተለመዱ በትዛዝ የሚሰቱ መድሀኒቶችን በቂ የሆነ መድሀኒት በእጅዎ ላይ እንዳለ ለማረጋገጥ እርምጃዎችን ይውሰዱ፤ አስፈላጊ የሆነ እንደሆነ እንደገማ መድሀኒቶችዎን ይሙሉ
• የሙቀት መለኪያ፣ ሶፍት እና የእጅ ማጽጃ ከታመሙ እና ቤት ሆነት ማገገም ሊያሰፈልግዎ የሚለች ከሆነ ይያዙ
• ከሚወዷቸው እና ከቤተሰብ አባላት ጋር እነዚህ ሰዎች ቢታመሙ ምን አይነት እንክብካቤ ሊያገኙ እንደሚችሉ እና ቤት ውስጥ እነርሱን ለመንከባከብ ምን ሊያስፈልግ እንደሚችል ይነጋገሩ
• ቤት ውስጥ ለሁለት ሳምንት የሚበቃ ውሀ እና ምግብ መቀመጡን ያረጋግጡ

ሌላ ላውቅ የሚያስፈልግ ነገር አለ?

• ማንኛውንም ሰው ከዘር እና የዘር የጀርባ ታሪክ ጋር ግንኙነት ባለው መልኩ አያግሉ። ቫይረሶች ሰዎችን በዘር፣ የህዝብ መገኛ እና የዘር የጀርባ ታሪክ መርጠው አያጠቁም።
• ሁልጊዜም መረጃ ይኑርዎ እንዲሁም ከአስተማማኝ ምንጭ መረጃዎችን መጠቀም ይቀጥሉ። ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎችን ኦንላይን እና ከሌላም ቦታ ቢሆን ይጠንቀቁ። በማህበራዊ ሚዲያዎችን የሚጋሩ የጤና መረጃዎች አብዛኛውን ጊዜ ትክክል ያልሆኑ ሲሆን፣ ይህም ከባለስልጣን፣ አስተማማኝ እንደ CDC፣ MDH ወይም አካባቢያዎ ዲፓርትመንት የሚመጣ ካልሆነ ነው።

ለሌሎች ቡድኖች ማለትም ለንግዶች የሚሆኑ ሌሎች ግብአቶች አሉ?

CDC ስለ COVID-19 ትክክለኛ የሆኑ መረጃዎችን በ cdc.gov ላይ ያቀርባል

ንግዶች

https://www.cdc.gov/coronavirus/2019-ncov/specific-groups/guidance-business-response.html

እርጉዝ ሴቶች፣ የሚያጠቡ እና ልጆች

https://www.cdc.gov/coronavirus/2019-ncov/specific-groups/pregnant-women.html

ትምህርት ቤቶች

https://www.cdc.gov/coronavirus/2019-ncov/community/schools-childcare/guidance-forschools.html

ተጓዦች

https://www.cdc.gov/coronavirus/2019-ncov/travelers/faqs.html

ሳምንታዊ እደሳዎች

ሳምንታዊ ኢሜይሎችን ስለ COVID-19 ለመግኘት ኢሜይልዎን ያሰገቡ እና “COVID-19” ብለው በ መተየቢያው ሳጥን ውስጥ ይጻፉ

https://tools.cdc.gov/campaignproxyservice/subscriptions.aspx?topic_id=USCDC_2067

Related:

LATEST UPDATE: Coronavirus Pandemic

Art in the Time of Coronavirus: Guide to Virtual Exhibitions from Ethiopia to U.S.

We Need Seismic Change, Right Now: by Marcus Samuelsson

City Sleeps: A Look At The Empty NYC Streets Amid The Virus – In Pictures

Ethiopia enforces 14-day quarantine for all travelers

Diaspora-based Tech Professionals Launch Ethiopia COVID-19 Response Task Force

Amid COVID-19 Pandemic Hopeful & Inspiring Stories Shared by Obama

Pleas to Diaspora to Assist Coronavirus First Responders in Ethiopia

Coronavirus Sparks an Epidemic of People Helping People in Seattle

Join the conversation on Twitter and Facebook. 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 


Copy Protected by Chetan's WP-Copyprotect.